Fana: At a Speed of Life!

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር ) የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ጎብኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስራዋን በኮፕ28 ጉባኤ ላይ ባለው የኢትዮጵያ አውደ ርእይ (ፓቪሊዮን) በማስተዋወቅ ላይ ትገኛለች፡፡

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ለአየር ጸባይ ለውጥ መከላከል እየከወነች ያለውን ተጨባጭ መፍትሄ የሚያሳየውን የአረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ መጎብኘታቸውን በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.