Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የተረጋጋ ሁኔታ ለመፍጠር ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ቅንጅት መጠናከር አለበት – አቶ ደሳለኝ ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ያጋጠመውን ችግር ለመፍታትና የተረጋጋ ሁኔታ ለመፍጠር ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ቅንጅት መጠናከር አለበት ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገለጹ።

በአማራ ክልል ኮማንድ ፖስት የጎንደር ቀጠና በወቅታዊ ስራዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

አቶ ደሳለኝ ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኮማንድ ፖስቱ እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ለውጦችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ገምግሟል ብለዋል።

ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ማህበረሰቡን ለበርካታ ችግሮችና እንግልት መዳረጉን ጠቅሰው፥ እስከ አሁንም ችግሩን መቅረፍና የተረጋጋ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መፍጠር አለመቻሉን አንስተዋል።

ለዚህም ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር መላላት ምክንያት መሆኑን በማንሳት፥ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታትና የተረጋጋ ሁኔታ ለመፍጠር ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ቅንጅት መጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ህብረተሰቡ ከገባበት ችግር እንዲወጣ ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመቆም ሊተባበር ይገባል ያሉት አቶ ደሳለኝ፥ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ፈተና ሆኗል ያሉት ሀላፊው፥ ችግሮችን በመነጋገርና ጥያቄዎችን በሰለጠነ አግባብ በማቅረብ መፍታት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰአትም ህብረተሰቡን ለማደናገር እየወጡ ያሉ የሀሰት መረጃዎች ማህበረሰቡን ለከፋ ችግርየሚያጋልጡ በመሆናቸው ቆም ብሎ ማሰብና ለሰላም መተባበር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በሙሉጌታ ደሴ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.