Fana: At a Speed of Life!

18ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦች ቀን ለማክበር እንግዶች ወደ ጂግጂጋ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ለማክበር እንግዶች ወደ ጂግጂጋ ከተማ እየገቡ ነው፡፡

18ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ በድምቀት እንደሚከበር ይታወቃል::

ከዛሬ ረፋድ ጀምሮም በዓየርና በየብስ የትራንስፖርት አማራጮች እንግዶች ወደ ጂግጂጋ ከተማ እየገቡ መሆኑን ነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ተረፈ በዳዳ የገለጹት፡፡

ለእንግዶቹም ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው ማለተታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የዘንድሮው በዓል በተለየ ሁኔታ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚከበር ጠቁመው÷ ሕዳር 25 የወንድማማቸነት ቀን፣ ሕዳር 26 የብዝኃነት ቀን፣ ሕዳር 27 የአብሮነት ቀን፣ ሕዳር 28 የመደመር ቀን እና ሕዳር 29 የኢትዮጵያ ቀን የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸው አብራርተዋል፡፡

በእያንዳንዱ ዕለትም ልዩ ልዩ ሁነቶች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.