የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከቤጂንግ አድሚኒስትሬቲቭ ኢንስቲቲዩት ጋር ሥምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲና የቤጂንግ አድሚኒስትሬቲቭ ኢንስቲቲዩት በጋራ ለመስራት ሥምምነት ተፈራረሙ።
የቤጂንግ አድሚኒስትሬቲቭ ኢንስቲቲዩት ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዝሃንግ ጁን የተመራ ልዑክ ባቱ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት በመገኘት ነው የጋራ ሥምምነቱን የተፈራረሙት።
የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ገረሙ ሁሉቃ (ዶ/ር) ኢንስቲቲዩቱ የሚሰጠው አገልግሎት እኛ ከያዝነው ተልእኮ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ የሥራ ሥምምነቱን በጋራ ፈርመናል ብለዋል።
የሁለቱ ተቋማት ልዑኮች በሰው ሀይል ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ስልጠና፣ በማህበራዊ ልማት አመራር እና በድህነት ቅነሳ ሥራዎች ላይ በጋራ ስለሚሰሩት ስራ ተወያይተዋል።
ለወደፊቱም በትምህርት፣ በስልጠና፣ በጥናትና ምርምርና መሰል ዘርፎች ለአምስት አመታት በጋራ ለመስራት በመስማማት የሁለቱ ተቋማት አመራሮች ፊርማቸውን በሰነድ አስፍረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!