ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል – አቶ መላኩ አለበል
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ ከሩሲያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ የረጅም ዘመናት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ከሩሲያ ልዑካን ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት፥ የሩሲያ ኩባንያዎች ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ሊሆን የሚችል የኬሚካል፣ የማሽነሪና የግብርና መሳሪያዎች እንዲሁም መኪና መገጣጠሚያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ለመሠማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና አባል ሀገር መሆኗ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚኖረውን ከፍተኛ ሚና ገልጽዋል።
ከ85 በመቶ በላይ የፋርማሲዩቲካል ምርት ከውጭ እንደሚገባ የጠቀሱት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም፣ ሀብትና ሰፊ የገበያ ዕድል ተገንዝበው ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሀገሪቱ የቡና ሀብትም በከፍተኛ ሁኔታ በጥሬው ወደ ውጭ እንደሚላክና እሴት ተጨምሮበት ወደ ሩሲያ ገበያ በሚገባበት ዙሪያ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪና ሌሎች በመንግስት በተገነቡ ትላልቅ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከፍተኛ አቅም ያላቸው የሩሲያ ኩባንያዎች በሚሰሩበት ሁኔታ ላይም ውይይት ማድረጋቸው ተመላክቷል።
የሩሲያ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲረዱ፣ በኢትዮጵያ በኩል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሩሲያ በኩል ደግሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በወኪሎቻቸው አማካኝነት የጋራ መድረክ በመፍጠር የማስተዋወቅና የሁለትዮሽ የቢዝነስ ግንኙነቱን የበለጠ ማጠናከር ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!