በሚዛን አማን ከተማ የተገጣጠመው ‘ሚዛን ትራክተር’ ስራ ላይ ዋለ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚዛን አማን ከተማ የተገጣጠመው ሚዛን የእርሻ ትራክተር ስራ ላይ መዋሉ ተገለፀ፡፡
ስያሜውን በሚዛን ከተማ ስም ያደረገው ይህ ትራክተር ከሚዛን አማን በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለማሰራጨት ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ስራ መገባቱ ተገልጿል።
ትራክተሩ በዳግም ኬኔዲ ጠቅላላ ንግድ ስራ ድርጅት የተገጣጠመ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ፥ የእርሻ ትራክተሩ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የጀመረችውን መነቃቃት በከፍተኛ ደረጃ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
በተለይም ‘ሚዛን ትራክተር’ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መገጣጠሙ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ የትራክተር እጥረትን የሚያስቀር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ከሚዛን ትራክተር በተጨማሪም በሚዛን ስም የተሰየሙ ጀኔሬተር እና የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለገበያ ለማስተዋወቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ከቤንቺ ሸኮ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡