ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጅግጅጋ ከተማ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችም ተገኝተዋል፡፡
በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡