የአየር ጤና ወለቴ መንገድ ግንባታ መካሄድ መጀመሩ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ጤና ወለቴ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የወሰን ማስከበር ስራ በተጠናቀቀባቸ ቦታዎች ላይ የግንባታ ስራ መጀመሩን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ የወሰን ማስከበር ስራው እየተከናወነ መሆኑን አመልክቷል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ታከለ ሉላና ለፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፤ የወሰን ማስከበር ስራ የተጠናቀቀባቸው ቦታዎች ላይ ግንባታ መካሄድ ጀምሯል።
መንገዱ 30 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ የሚገነባ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ይህም የትራፊክ መጨናነቁን ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ነው ኢንጀነር ታከለ ሉላና የተናገሩት።
የመንገዱን ግንባታ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ መታቀዱም ተገልጿል፡፡
መንገዱ ከአምስት ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያለው ሲሆን ከ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል።
በዙፋን ካሳሁን