የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስገዝ ስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ ሰነድ ለባለድርሻ አካላት ውይይት ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስገዝ ስትራቴጂክ እቅድ ረቂቅ ሰነድ ለባለድርሻ አካላት ውይይት ቀረበ፡፡
በውይይት መድረኩ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ÷ የአምስት ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት ሒደትና ዘጠኝ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለባለድርሻ አካላት አቅርበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ የሴክተር መስርያ ቤት አመራሮች እና የኢንዱስትሪ ተቋማት ሃላፊዎች በስትራቴጂክ ዕቅዱ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
ረቂቅ ሰነዱ ዩኒቨርሲቲው ወደ ሙሉ ራስ ገዝነት የሚያደረገውን የሽግግር ሒደት ማሳካት የሚያስችለውና የሚያረጋግጥበት መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ተሳታፊዎች የአምስት ዓመት ዕቅዱ የባለድርሻ አካላትንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ፍላጎት ያገናዘበ እንደሆነ መናገራቸውንም የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!