Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከ5 ሚሊየን በላይ መፅሐፍት መሰራጨቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመማር ማስተማር ተግባሩ የሚረዱ 13 ነጥብ 6 ሚሊየን መፅሐፍትን ለማሰራጨት ታቅዶ እስካሁን 5 ነጥብ 3 ሚሊየን መጽሐፍት ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰራጨቱን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
 
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግስቱ እንደገለጹት፤ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 918 ሺህ 76 መፅሐፍት ተሰራጭቷል።
 
3 ሚሊየን መጽሐፍት በክልሉ ባለው የጸጥታ ሁኔታ የተነሳ ማሰራጨት አለመቻሉን ጠቁመዋል።
 
ለአንደኛ ደረጃ 7 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚሆን መፅሃፍት ከውጭ ታትመው የገቡ መሆኑን ገልፀው፤ በመጋዘን የተቀመጡትን መጽሐፍት በማከፋፈል ለመማር ማስተማር ተግባሩ እንዲውሉ ይደረጋል ብለዋል።
 
በክልሉ 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመቀበል ታቅዶ 3 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑትን መመዝገብ የተቻለ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ ለማስጀመር እንደሚሰራ ተናግረዋል።
 
በተያያዘ በክልሉ 75 ሚሊየን ብር በመመደብ የትምህርት ቤቶች ምገባ ስርዓት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።
 
በክልሉ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመመገብ ታቅዶ ወደ ተግባር ቢገባም እስካሁን 200 ሺህ የሚሆኑትን ብቻ ተጠቃሚ መሆናቸውን ወ/ሮ እየሩስ ገልፀዋል፡፡
 
ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ ለማፍራት እንዲቻል አስፈላጊ የሆነውን የትምህርት ቤት ምገባ በታቀደው ልክ እንዳይፈጸም የተለያዩ እንቅፋቶች ማጋጠማቸውን ተናግረዋል።
 
በዚህ ዓመትም 844 ሺህ ጎልማሶችን ለማስተማር ታቅዶ በተሰራው ስራ መፈጸም የተቻለው 28 በመቶ ብቻ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ እየሩስ፤ መንግስቱ በየዓመቱ ዕቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር ቢገባም እስካሁን ግን አፈፃፀሙ ዝቅተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
 
የሰለጠኑ ባለሙያዎች ቅጥር አለመፈፀም፣ የቅንጅት አለመኖርና ጥብቅ ክትትል አለማድረግ ለአፈፃፀሙ ዝቅተኛ መሆን እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡
ችግሩን ለመፍታት ሰነድ ተዘጋጅቶ ከአጋር አካላት ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
 
በሰብለ አክሊሉ
#Ethiopia
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.