Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ የፈረሙት ስምምነት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳለው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ የተፈራረሙት ስምምነት ግንኙነታቸውን የሚያጠናክር እና ዘረፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ፡፡
 
የሕግ ምሁር እና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ተንታኙ ማሩ አብዲ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ የባሕር በርን ለሶማሊ ላንድ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ያስገኛል ብለዋል፡፡
 
የሁለቱ ወገኖች እዚህ ስምምነት ላይ መድረስም ለኢትዮጵያ እንደ ትልቅ ዲሎማሲያዊ ድል ይቆጠራል ነው ያሉት፡፡
 
ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ዓለም ዓቀፍ ሕግን፣ ዕኩልነትን እና አብሮ መልማትን መሠረት ያደረገ አካሄድ መከተሏ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል እንድትጎናፀፍ እንዳስቻላትም ነው የጠቀሱት፡፡
 
በዓለም መድረክ የድርድር አቅም የሚለካው ከጎረቤት ሀገራት ጋር ባለ መስተጋብር፣ በማምረት አቅም፣ በቀጣናው ብሎም በሀገር ውስጥ ባለ ሰላምና መረጋጋት ጋር የሚያያዝ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
 
ከሶማሊ ላንድ ጋር የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ስብራት የሚጠግንና ፍላጎቷን የሚመልስ ከመሆኑም በላይ በዓለም መድረክ መፈለግና የድርድር አቅሟን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።
 
ኢትዮጵያ በታሪክ እና በተፈጥሮ የሚገቧትን ለማግኘት ዲፕሎማሲያዊ መርሆችንና የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊነት ያከበረ መንገድ ተከትላ የምታደርገውን ጥረት ይበልጥ ተቋማዊ ማድረግ እንዳለባትም መክረዋል፡፡
 
የኢትዮጵያን ብልጽግና ዕውን ለማድረግም ማምረት እና መሸጥ አንዱ መንገድ መሆኑን ጠቁመው፥ ሁሉም ዜጋ ተደራጅቶ ባገኘው መድረክ ሁሉ የኢትዮጵያን ፍላጎት ለዓለም ማሳወቅ፣ የምንፈልገውን እና የተገባንን መጠየቅ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡
 
በመራኦል ከድር
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.