አብርሆት ቤተ መጻሕፍት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተ መጻሕፍት የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ።
አብርሆት ቤተ መጻሕፍት ማዕድ ያጋራው በከተማው ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና የጎዳና ተዳዳሪዎች መሆኑ ተገልጿል።
በማዕድ ማጋራት መርሃግብሩ ላይ የተገኙት የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር ውባየው ማሞ (ኢ/ር) እንደገለፁት÷ መሰል በዓልን ስናከብር አንዱ ለሌላው ያለውን በማካፈልና በልግስና ሊሆን ይገባል ብለዋል።