Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የተለያዩ የእምነት አባቶች ታቦት የሚያልፍበትንና የሚያድርበትን ስፍራ አጸዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9 2016 (ኤፍ ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ የእምነት አባቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች ታቦት የሚያልፍበትንና የሚያድርበትን ስፍራ አጸዱ።

 

የከተራና የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በድምቀት ይከበራል።

 

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ሒክማ ኸይረዲን፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ የእምነት አባቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች ዛሬ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ታቦት የሚያልፍበትንና የሚያድርበትን ስፍራ አጽድተዋል።

 

በዚሁ ወቅት ወይዘሮ ሒክማ እንዳሉት÷ ጥምቀት ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው።

 

በዓሉ በባለቤትነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይከበር እንጂ ሃብትነቱ የመላው ኢትዮጵያውያን ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

በመሆኑም ነገና ከነገ ወዲያ የሚከበሩትን የከተራና የጥምቀት በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ መላው የመዲናዋ ነዋሪ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

 

ሰላም ወዳዱ የከተማዋ ነዋሪ በተለመደው ጨዋነት በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.