Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ባከናወናቸው የውጭ ጉዳይ ስራዎች ጫናዎች መቋቋም ተችሏል – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መንግስት ባከናወናቸው የውጭ ጉዳይ ስራዎች ኢትዮጵያን ያጋጠሟትን ጫናዎች መቋቋም ችላለች አሉ፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

ፕሬዚዳንት ታዬ የመንግስት ዓመታዊ የትኩረት አቅጣጫን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር÷ የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂካዊ ምርጫ በመደርጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

የውጭ ግንኙነት መነሻው ብሔራዊ ጥቅም እና ዜጎች ክብር ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ሁለቱን መሰረታዊ ጉዳዮች ለማሳካት መንግስት ጥረት ማድረጉን ገልፀዋል፡

ከነዚህ ብሔራዊ ጥቅሞች አንዱ የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የባህር በር ጥያቄ መሆኑን አንስተው፤ በ2017 በጀት ዓመት ጥያቄው በዓለም አቀፍ ተቋማት ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

መንግስት ባከናወናቸው የውጭ ጉዳይ ስራዎች ኢትዮጵያን አጋጥሟት የነበረውን ዘርፈ ብዙ ጫና በመቋቋም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ግንባታን ማጠናቀቅ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም መንግስት ባከናወናቸው ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ በተለያ ሀገራት በእንግልት ላይ የነበሩ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

እንዲሁም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የተከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታት ሀገራዊ ምክክር ተቋቁሞ ዜጎች አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን አውስተዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.