Fana: At a Speed of Life!

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ጥረቶች ስኬት እያመጡ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ጥረቶች ስኬት እያመጡ ነው አሉ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፡፡

ለሦስት ቀናት የሚቆየው የግብርና ሚኒስቴር፣ ተጠሪ ተቋማቱና የክልሎች የ6 ወራት የግብርና ዘርፍ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በግምገማ መድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ አርሶና አርብቶ አደሮች ከቀረጥ ነፃ የሆነ ትራክተርና ኮምባይነር በማግኘት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራትም በሁሉም የግብርና ዘርፎች ትልቅ ውጤት ተመዝግቧል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመኸር ወቅት 17 ነጥብ4 ሚሊየን ሄክታር መልማቱን ገልጸው÷ በአሁኑ ወቅትም ከ90 በመቶ በላይ ምርት መሰብሰቡን አስታውቀዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.