Fana: At a Speed of Life!

የከተሞች የመንግስት ተቋማት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 9ኛው የከተሞች የመንግስት ተቋማት ጉባኤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

 

በጉባኤው የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም  ግምገማ ተካሂዷል፡፡

 

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ የከተሞች መሠረተ ልማት፣ የአረንጓዴ መሠረተ ልማት፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የአሠራርና አደረጃጀት ስራዎችን ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች ለውጦች እየተመዘገቡ ነው፡፡

 

ለአብነትም በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  አነሳሽነት የተከናወኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶችና የመልሶ ማልማት ስራዎችን ጨምሮ፣ የከተሞች ልማታዊ ምግብ ዋስትና፣ የቤት ልማት አማራጮች እንዲሁም በከተሞች ፎረም ዝግጅት በተደረጉ ርብርቦች የተገኙ ውጤቶችን አንስተዋል፡፡

 

በቀጣይ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን በማዘመንና አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል  የሚጠበቁብንን ኃላፊነቶች በበለጠ  ጠንካራ ብሔራዊ እና ተቋማዊ ሥነ ልቦና ውስጥ በመሆን በጋራ መወጣት ይጠይቃል ብለዋል።

 

በቤዛዊት ከበደ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.