Fana: At a Speed of Life!

የፖላንድ የሕክምና ባለሙያዎች በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ ሕክምና እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖላንድ የሕክምና ባለሙያዎች ልዑክ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የሕክምና አገልግሎተ እየሰጠ ነው፡፡

በልዑካኑ ውስጥ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ፣ የዩሮሎጂ ሕክምና ፣ የኒውሮ ሰርጀሪ ሕክምና ፣ የሰመመንና የነርስ ባለሙያዎች ቡድን እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ባለሙያዎቹ ከሆስፒታሉ የማህፀንና ጽንስ ሕክምና ቡድንና ከዩሮሎጂ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ጋር ክትትል ለሚያደርጉ ታካሚዎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በነጻ ሕክምና አገልግሎቱ እስካሁን 12 ታካሚዎች ቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው መሆኑን የሆስፒታሉ መረጃ ያመላክታል፡፡

እስከ ዓርብ ባሉት ቀናትም ለዘጠኝ ታካሚዎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመስጠት በአጠቃላይ 21 ሰዎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡

የዩሮሎጂ የቀዶ ሕክምና ቡድን በተመሳሳይ ቀናት ባደረገው የዩሮሎጂ የኩላሊትና ፊኛ ቀዶ ሕክምና ከ6 በላይ ታካሚዎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት አግኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.