የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ፡፡
ከሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) በተጨማሪ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ለገሰ እና የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አምባሳደር አሊ አብዶ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ወቅትም÷ አባቶቻችን የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚመጥን መታሰቢያ በዚህ መልኩ ተገንብቶ በማየታችን ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡