Fana: At a Speed of Life!

የአፍጥር እና የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) የረመዳን ወርን በማስመልከት “ኢትዮጵያ ታፍጥር” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባና በተመረጡ የክልል ከተሞች የአፍጥር እና የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር ሊካሄድ ነው፡፡

የማዕድ ማጋራቱ የሚከናወነው በረመዳን ቀናት ሲሆን÷ በጎዳና ላይ ለሚኖሩ፣ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ፣ በሕክምናና በማረሚያ ቤት ለሚገኙ እና የአልጋ ቁራኛ ለሆኑ ወገኖች መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ-ጥበብ ሥነ-ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ነፊሳ አልመሃዲ እንዳሉት÷ ከበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር በመተባበር ዘይት፣ ዱቄት፣ ሩዝ እና የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያዎችን ለመለገስ ታቅዷል፡፡

ለዚሁ ድጋፍ የሚውለው ገቢም ከለጋሽ ተቋማትና ግለሰቦች ይሰበሰባል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም ከ72 ሚሊየን በላይ ገቢ በማሰባሰብ ከ90 ሺህ የሚልቁ ወገኖችን ለመድረስ ታስቧል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.