በዓለም አቀፉ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እየተሳተፉ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ሶቺ ከተማ እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉ ይገኛል።
በፌስቲቫሉ ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ20ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሳተፋ ይገኛል።
በዚህ ፌስቲቫል ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም እየተሳተፋ ሲሆን÷ መድረኩ ወጣቶች ሀገራቸውን እንዲያስተዋውቁ እና እርስ በእርስ ልምድና ተሞክሯቸውን እንዲለዋወጡ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ መገለፁን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቲቫሉ ጎን ለጎን የባህል፣ የስፖርት፣ የሙዚቃ፣ የፋሽንና የዲዛይን ትዕይንቶች እየተካሄዱ መሆኑ ተገልጿል።
ይህም የኢትዮጵያን የቡና ስርዓትን ጨምሮ ሌሎች እሴቶችን ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ ፋይዳው የጎላ መሆኑም ታምኖበታል፡፡
ፌስቲቫሉ ከፈረንጆቹ መጋቢት 1 እስከ 7 ቀን 2024 ድረስ የሚቆይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡