የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ምክንያት የተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ የተቋረጡ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ ማጋጠሙን የገለጸው ባንኩ፤ አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር እየጣረ መሆኑን ገልጿል።
በመሆኑም ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል።