ክልሎች የተመጣጠነ እድገት እንዲኖራቸው ጠንካራ የጋራ ገቢ አስተዳደር ሥርዓት ያስፈልጋል – አፈ ጉባዔ አገኘሁ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት እንዲኖር የገቢ ክፍፍልና ማስተላለፍ ቀመር ግልጽና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት ሲሉ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
የጋራ ገቢዎች አስተዳደር ክፍፍልና ማስተላለፍን በተመለከተ የፌዴሬሽን ም/ቤት በሃዋሳ ከተማ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።
አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በመድረኩ እንዳሉት÷ ክልሎች እኩል አልያም የተመጣጠነ እድገት እንዲኖራቸው ጠንካራ የጋራ ገቢ አስተዳደር ሥርዓት ያስፈልጋል።
በተለይ የማዕድንናትላልቅ ሃብቶች ገቢ አስተዳደር ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ መተዳደር እንዳለበት አስገንዝበው፤ መንግስት ለዚህ ትኩረት ሰቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በጥላሁን ይልማና ሀና በየነ