Fana: At a Speed of Life!

ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ተጀምሯል፡፡

አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ከተማ የተመደቡ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ከአዲስ አበባ የሰላም ሠራዊት ጋር በማስተሳሰር ነው የተጀመረው፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)÷የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በማሰባሰብ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ተቀርጾ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልፀዋል፡፡

የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ለሀገር ግንባታ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ነው የተናገሩት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው÷አገልግሎቱ በማህበራዊ ትስስር፣ በልማት ሥራዎችና በማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ እንደሚያተኩር ተናግረዋል፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልገሎቱ የተመደቡ ተማሪዎችን ከአዲስ አበባ የሠላም ሰራዊት ጋር በማስተሳሰር ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ካሉ አደረጃጀቶች ጋር እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

ተማሪዎች በበኩላቸው÷ተግባሩ አብሮነትን ለማመጠናከር እንዲሁም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማጉላት ጠንካራ ሀገረ-መንግስት ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንዳለው መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.