Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ዘመናዊና ፕሮፌሽናል ሰራዊት መገንባት መቻሏን ተረድተናል – የሞሮኮ ም/ጠ/ ኢታማዦር ሹም

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ዘመናዊና ፕሮፌሽናል ሰራዊት መገንባት መቻሏን መረዳታቸውን የሞሮኮ ምክትል ኢታማዦር ሹም ሜጀር ጀኔራል አዚዝ እድሪስ ተናገሩ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ(ኢ/ር) በሞሮኮ ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል አዚዝ ኢድሪሲ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ሜ/ጄ አዚዝ ኢድሪሲ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ተቋማትን እንደጎበኙ ገልፀው÷በዚህም ኢትዮጵያ ዘመናዊና ፕሮፌሽናል ሰራዊት መገንባት መቻሏን መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡

በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ባደረጉት ጉብኝት ሰፊ ልምድ መቅሰማቸውንና በቆይታቸው ለተደረገላቸው መልካም አቀባባል ምስጋና ማቅረባቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) በበኩላቸው ÷በሞሮኮና በኢትዮጵያ መካካል ያለው ግንኙነት ታሪካዊና የቆየ መሆኑን አውስተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ጉብኝትም ይህንን ግንኙነት በወታደራዊ እና በሌሎች መስኮች ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ቦታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.