Fana: At a Speed of Life!

ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት መጀመሩን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዛሬው እለት በመናኸሪያዎች አካላዊ ርቀትን ለማስጠበቅ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል ተጠቃሚዎች ትኬት ለመቁረጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚፈጠር አካላዊ ጥግግት ለመቀነስ የሚረዳ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት ክፍያ አገልግሎት በይፋ ተጀምሯል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አግልግሎቱ በይፋ በተጀመረበት ወቅት ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖርት ክፍያ ስርዓት ወረርሽኙን ከመከላለከል ጎን ለጎን ዘርፉን በቴክኖሎጂ አስደግፎ በመምራት እና የተጠቃሚውን የጊዜ፣ የጉልበትና የገንዘብ ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

የአገልግሎት ስርዓት አሰጣጡ ተጓዞች ወደ መናኸሪያ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ባሉበት ሆነው ትኬት መቁረጥ የሚያስችል መሆኑን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.