ግብፅ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃወሙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃውመውታል።
የአረብ ሊግ አባል ሀገራት በዛሬው እለት ስብሰባቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የአረብ ሊግ በስብሰባው ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብን ጨምሮ የሊቢያ ጉዳይንም በመመልከት ላይ ይገኛል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው የቪዲዮ ኮንፍረንስ ላይ ሀገራቸው በግብዱ ዙሪያ የያዘቻቸውን የውሳኔ ሀሳቦች አቅርበዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ እያካሄዱት ባለው ድርድር ከስምምነት ሳይደርስ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሞላት እንዳይጀምር የሚል ተካቶበታል።
የአረብ ሊግ አባል ሀገራት ግብፅ የህዳሴ ግድብ ጉዳይን ወደ ፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷንም እንዲደግፉ የጠየቀች ሲሆን፥ ግብጽ በናይል ወንዝ ላይ የተፈጥሮ መብት እንዳላት ማስረገጥ የሚሉትም ተጠቃሽ ናቸው።
በዚህ ስብሰባ ላይም የሊጉ አባል ሀገራት የሆኑት ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር የግብፅን ከታላቁ የውሳኔ ሀሳብን እንደማይቀበሉት አስታውቅዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።