Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 250 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ8ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 414 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 250 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ ፡፡

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ቫይረሱ የተገኘባቸው 158 ወንድ 92 ሴቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 177 አዲስ አበባ፣ 21 ትግራይ ክልል፣ 20 አማራ ክልል፣ 18 ጋምቤላ ክልል፣ 8 ኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሶማሌ ክልል፣ 1 ድሬዳዋ እና 1 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በትናንትናው እለት የ8 ሰዎች ህይወት (7 ከአዲስ አበባ እና 1 ከድሬዳዋ) ማለፉም ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 89 ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 144 ሰዎች (123 ከአዲስ አበባ፣ ከአማራ እና ትግራይ ክልሎች ሰባት ሰባት፣ ከሶማሌ ክልል 5 እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል 2) ከቫይረሱ ሲያገግሙ በአጠቃላይ 1 ሺህ 688 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እስካሁን ለ237 ሺህ 464 ሰዎች የለቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሺህ 425 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.