የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ ትራንስፎርመር በክሬን የጫኑ ግለሰቦችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ የሆነ ትራንስፎርመር በክሬን ጭነው ለማምለጥ የሞከሩግለሰቦችን እሰከጫኑበት ክሬን እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ግለሰቦቹ በቦሌ ክክፍለ ከተማ ከተማ ወረዳ 10 ሐያት ቁጥር 1 በሚባል አካባቢ በትናንትናው እለት ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 አካባቢ ለ80 አባወራዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ትራንስፎርመር ከመስሪያ ቤቱ ዕውቅና ውጭ በክሬን ተሸከርካሪ ታግዘው በመስረቅ ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪ ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክቶሬት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ገልዋል።
ግለሰቦቹ በኃላፊያቸው ታዘው ትራንስፎርመር ለመቀየር መምጣታቸውን ቢናገሩም በኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የኮንስትራክሽንና ሜንቴናንስ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ሰርሞሎ ግለሰቦቹን መሥሪያ ቤቱ እንደማያውቃቸውና ከመሥሪያ ቤቱ የታዘዙ ቢሆኑ እንኳን የትዕዛዝ ደብዳቤ መያዝ እንደነበረባቸው ገልፀዋል።
ለማነኛውም ትዕዛዝ ሰጥቶናል እንድንሰራ ያሉትንም ሓላፊ ከፖሊስ ጋር በጋራ እንደሚያጣሩት በበኩላቸው አስረድተዋል።
ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን ለመቀጠል ተጠርጣሪዎቹንና በእግዚቢትነት የተያዙ ንብረቶችን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ መጀመሩን የገለጹት ኮማንደር ያሲን ሁሴን፥ በመብራትና በሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበት ጥጭሪ አቅርበዋል።
የመብራት ኃይል ሰራተኞች ነን በሚል የሚመጡ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ህጋዊ ሰራተኞች ስለመሆናች በአግባቡ ማረጋገጥ ይኖርበታል ሲሉ ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።