Fana: At a Speed of Life!

በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)በእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ጂን ሊኩን የተመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ።

የልዑካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም ከአየር መንገዱ አመራር አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርጓል።

ከውይይቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አጠቃላይ የስራ እስቅስቃሴ ተዘዋውሮ መጎብኘቱን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.