Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓት የሥራ ባሕል የመዲናዋ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተፋጠነ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የ24 ሰዓት የሥራ ባሕል የኮሪደር ልማት ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ ነው አሉ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በኮሪደር ልማት ስራ ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓታት እየተጉ የሚገኙ ታታሪ ሰራተኞችን ማዕድ በማጋራት አበረታተናል ብለዋል።

በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች በኮሪደር ልማት ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሰራተኞች ሌት ተቀን በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት ከንቲባዋ፥ በዚህም የኮሪደር ልማት ሥራው እየተፋጠነ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው ሰራተኞቹ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት ለከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያበረከቱት ላለው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም እነዚህን ሰራተኞች ለማበረታታት በተዘጋጀው የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር የተሳተፉ ባለሀብቶችን አመስግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.