Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)  የሹመት ደብዳቤያቸውን ለቱርክሜኒስታን መንግስት አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፓኪስታን የኢፌዲሪ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት  አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ለቱርክሜኒስታን የፓርላማ አፈ-ጉባኤ  ዱንያጎዜብ ጉልማኖቫ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል።

 

በዚሁ ወቅት አምባሳደር  ጀማል ከፕሬዚዳንት  ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተላከውን መልካም ምኞት ለፓርላማ አፈ-ጉባኤ አድርሰዋል::

 

የኢትዮጵያን ጠንካራ ሀገርነት የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆን ፓን-አፍሪካኒዝም እያቀነቀነች ለዘመናት በአፍሪካ ሀገራት መካከል ወንድማማችነትና ትብብር እንዲጐለብት እያደረገች ያለውን ጥረት አስረድተዋል።

 

አምባሳደር ጀማል በከር(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተወሰዱትን የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ የህግ ማዕቀፍና የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሞች መካሄዳቸውንም አስረድተዋል፡፡

 

ይህም በተለያዩ የኢኮኖሚ መስኮች በኢትዮጵያ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች አማራጭ የቢዝነስ ዕድሎች የፈጠረ እንደሆነ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

 

የቱርክሜኒስታን ፕሬዚዳንትን በመወከል የሹመት ደብዳቤ የተቀበሉት የፓርላማ አፈ-ጉባኤ ዱንያጎዜብ ጉልማኖቫ በበኩላቸው÷ሁለቱን ሀገራት በተለያዩ የሁለትዮሽ መስኮች በማቀራረብ በአጋርነት ለመስራትና ግንኙነቱን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.