Fana: At a Speed of Life!

መዲናዋ ከፈረንሳይ ከተሞች ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች ጋር ያላትን የጠበቀ ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቅርብ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜይክ ጋር በልዩ ልዩ የትብብር መስኮች ዙሪያ በሚኖር የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ መክረዋል፡፡

ውይይቱን አስመልክቶ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ በተመሰረተው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲሁም የፈረንሳይ መንግስት በከተማችን በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ዙሪያ ስለሚያደርገው ድጋፍ ከአምባሳደር ላሜይክ ጋር የተወያይተናል ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች ጋር ያላትን የጠበቀ ወዳጅነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያም ተነጋግረናል ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.