Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ እና ድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የገናበዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

የገና በዓል ሲከበር የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌነት በመከተል የሰላም ዕሴቶችን በመገንባት፣ ፍቅርን እና አብሮነትን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስገንዝበዋል፡፡

ከንቲባ ከድር በበኩላቸው በዓሉ ሲከበር በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን ይባል ብለዋል፡፡

ከንቲባዎቹ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት÷ በዓሉ  የመደጋገፍና የመተጋገዝ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.