አየር መንገዱ 558 የአቪዬሽን ባለሙያዎችን አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትየጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ 558 የአቪዬሽን ባለሙያዎች ማስመረቁን አስታወቀ።
በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተደረገው የምርቃት ስነ ስርዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን ጨምሮ የአቪዬሽን ባለድርሻ አካላት፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተሳትፈዋል፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ለተመራቂዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው በዚህች ልዩ ቀን ወረርሽኙ እንድንሰበሰብ ባይፈቅድም በዚህ መልኩ ለማክበር ችለናል ብለዋል፡፡
አያይዘውም የተማረ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለዘላቂ ልማት ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከል 72 አብራሪዎች፣ 173 የበረራ አስተናጋጆች፣ 7 የአውሮፕላን ቴክኒሻኖች ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ውጭ የስድስት ሃገራት ዜጎች መመረቃቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡