ርዕሰ መስተዳድሮች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ለጥምቀት በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መልካም በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።
በተመሳሳይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ለከተራ እና የጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም በዓሉን ስናከብር አንድነታችንንና አብሮነታችን የሚያጎሉ ነባር እሴቶችን በማጠናከር መሆን አለበት ብለዋል።