Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ አንድነትን የሚያጠናክር የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት ተፈጥሯል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር፣ ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት መፈጠሩን ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ፥በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያው ጉባዔው አቅጣጫ መነሻ በክልሉ በተከናወኑ የሠላምና ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሁም አጠቃላይ በተገኙ የፖለቲካ ድሎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም÷በክልሉ ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር የተረጋጋ የፖለቲካ ሥረዓት በመዘርጋት ለሠላምና ለልማት ሥራዎች ምቹ መደላድል መፈጠር መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም ባለፉት ሶስት ዓመታት በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን መፈጸም መቻሉን ነው ያስረዱት፡፡

በክልሉ ምሥረታ ወቅት በአንዳንድ የክልሉ አከባቢዎች የነበረው የሠላም እጦት በህብረተሰቡና በፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅት ወደተሟላ ሠላም ማሸጋገር ተችሏል ብለዋል፡፡

በተለይም በአርብቶ አደር አከባቢ የሚስተዋለውን የፀጥታ ስጋት በመፍታት አዎንታዊ ሠላም መገንባት መቻሉን ገልጸዋል።

ክልሉ ድንበር በሚጋራበት የደቡብ ሱዳን ቀጣና የሚስተዋለውን የፀጥታ ስጋት የመቅረፍ እንዲሁም ከክልሉ ጋር በሚዋሰኑ አጎራባች ክልሎች ጋር የጋራ የፀጥታ ፎረም በማዋቀር በወንድማማችነት መርሕ ላይ ችግሮችን የመፍታት ተግባር መከናወኑን አንስተዋል፡፡

ቡናን ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ መጠን ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ክልሉ የበኩሉን ሚና እየተወጣ እንደሆነ መናገራቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.