ፕሬዚዳንት ታዬ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የጋምቢያ አምባሳደር አሰናበቱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የጋምቢያ አምባሳደር ጃይናባ ጃግኔን አሰናበቱ፡፡
በኢትዮጵያ እና ጋምቢያ መካከል ያለው ግንኙነት በማጠናከር ረገድ አምባሳደሩ ላበረከቱት ሚና ፕሬዚዳንቱ አመሥግነዋል፡፡
በቀጣይም በሀገራቸው በሚኖራቸው ኃላፊነት የሀገራቱን ግንኙነት በይበልጥ ለማጠናከር በትጋት እንዲሠሩ ጠይቀዋል፡፡