Fana: At a Speed of Life!

ሕብረቱ የአህጉሪቱን ተሰሚነት ለማሳደግ የፋይናንስ አቅሙን ማጠናከር አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የአህጉሪቱን ተሰሚነት ለማሳደግ የፋይናንስ አቅሙን ማጠናከር ይጠበቅበታል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡

የአባል ሀገራቱ ብቁ የፋይናንስ ምንጭ አለመሆን ለሕብረቱ ሉዓላዊነት መጣስ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ምሁራኑ አመላክተዋል፡፡

ይህም ሕብረቱ በተለያዩ ጊዜያት አጀንዳዎችን ቀርፆና አደራጅቶ ይወያይባቸው እንጂ መሬት እንዳይወርዱ ማድረጉን ነው የሕግ ባለሙያና ተማራማሪ የሆኑት ማሩ አብዲ የተናገሩት፡፡

ይህን ለመፍታት ቀዳሚው አማራጭ ሕብረቱን የሚያጠናክር በራስ አቅም የሚንቀሳቀስ አህጉራዊ ተቋም መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ በፍቃዱ ዳባ አስገንዝበዋል፡፡

አህጉሪቱ ያላትን የሰው ኃይልና የተፈጥሮ ሀብት መጠቀም ያስችል ዘንድ ምቹ የኢንቨስትመንት ምኅዳር በአህጉሪቱ ሊፈጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.