Fana: At a Speed of Life!

240 ሺህ ሄክታር ውሃማ አካላት ላይ መጤ አረምን የማስወገድ ሥራ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 240 ሺህ ሄክታር ውሃማ አካላት ላይ የሚታይ መጤ አረምን የማስወገድ ሥራ መከናወኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ደረቅ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም፣ የሥርዓት ምህዳርና የደህንነተ ሕይወት ጥበቃና ቁጥጥር እንዲሁም ዓለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነት ትግበራ ላይ ክትትል በማድረግ ውጤታማ ሥራ መከናወኑ ተገልጿል፡፡

በግማሽ ዓመቱ የ203 ከተሞች የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፣139 የፕላስቲክ አምራች ፋብሪካዎችና 671 ናሙና ቦታዎች ላይ የድምጽ ልኬት መከናወኑ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በ140 የውሃማ አካላት ላይ የናሙና ልኬት በማድረግ የክትትልና የድጋፍ ሥራዎች መከናወናቸውን የባለስልጣኑ መረጃ አመልክቷል፡፡

ከ240 ሺህ ሄክታር ውሃማ አካላት ላይ የሚታይ መጤ ወራሪ አረምን ማስወገድ መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡

ከ6 ሺህ 500 በላይ ነባር ፕሮጀክቶች ላይ የአካባቢና ማህበረሰብ ተፅዕኖ ግምገማ በማድረግ ይሁንታ መሰጠቱ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.