Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ዓመት ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ በ2017 ግማሽ ዓመት ከ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዙን አስታወቀ፡፡

የመምሪያው አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ የ6 ወር የሥራ አፈፃፀም የማጠቃለያ ግምገማ ላይ እንዳሉት፥ የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የፌደራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ነው፡፡

ከተያዙት ዕቃዎች መካከል ተሽከርካሪዎች፣ መድኃኒቶች፣ የከበሩ ማዕድናት፣ በሰው ጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን እና ምግቦች እንደሚገኙበት መገለጹን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.