Fana: At a Speed of Life!

በተስፋ ብርሃን ምገባ ከ36 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 19 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች የሚቀርበውን የምገባ አገልግሎት ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ እንዳሉት÷ በአዲስ አበባ ከሚተገበሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች መካከል ተስፋ ብርሃን ምገባ አንዱ ነው።

በዚህም በመዲናዋ ከፍተኛ ድጋፍ የሚሹ የሕብረተሰብ ክፍሎች በቀን አንዴ የምገባ አገልግሎት እያገኙ ነው ብለዋል።

አሁን ላይም ከ36 ሺህ በላይ ዜጎች በ22 ማዕከላት የምገባ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

በቀጣይ በመዲናዋ በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች የሚቀርበውን ምገባ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

የምገባ ማዕከላቱን ለማስፋፋትም ባለሃብቶች እና አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቅርበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.