Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ካቢኔው በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው የዓቃቢያነ-ሕግ የጥቅማ ጥቅም ማሻሻያ ጥናት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

እንዲሁም ሰፋፊ የስራ እድል ለሚፈጥሩ እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ አምራች ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ግንባታ እና ለማስፋፊያ የቀረበ የመሬት ጥያቄ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ተፈፃሚ እንዲሆን ውሳኔ ማሳለፉን የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.