በሐረሪ ክልል ለ41 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 41 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡
የክልሉ የኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ እስማኤል ዩሱፍ÷ በግማሽ ዓመቱ በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ለ4 ሺህ 822 ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ለኢንተርፕራይዞች ከ35 ሚሊየን ብር በላይ የብድር አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸዋል።
በክልሉ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 41 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደተሰጠ መጠቆማቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የጥሬና የፋብሪካ ውጤቶች የግብዓት አቅርቦትን ለማሻሻል 287 ቶን በላይ ግብዓት ማቅረብ መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡