Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ የ5ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ፈጣን የሆነውን የ5ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በጅማ ከተማ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በዚህ ወቅት÷ ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግና የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ ማዘመን የሚያስችል ቴክኖሎጂን እያበሰረ ይቀጥላል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በተከናወነ ሥራም የቴሌ ብር አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ 12 ከተሞችን የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ማቻሉን አንስተዋል፡፡

በወርቃፈራሁ ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.