Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባዔው የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ጉባዔው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸምላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡

በጉባዔው የአስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማው ምክር ቤት አባላት እና የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.