Fana: At a Speed of Life!

ስፔን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የልማት አጋርነት ለማስፋት ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔን ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ያላትን የልማት አጋርነት ለማስፋት በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ገለፀች፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ከስፔን ዓለማቀፍ የልማት ትብብር ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አንቶን ሌይስ ጋርሺያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ ፥ የስፔን መንግስት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲያገግም እና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

መንግስት የሀገር ውስጥ ገቢን በማጠናከር፣ በምግብ ራስን በመቻል እንዲሁ በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ኢኮኖሚውን እያሻሻለ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

አንቶን ሌይስ ጋርሺያ በበኩላቸው ÷ ቀደም ሲል በሁለቱ ሀገራት መካከል በሁለንተናዊ የጤና ሽፋን፣ በገጠር ልማት ዘርፍ እና በጾታ እኩልነት ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙን አስታውሰዋል፡፡

በተፈረሙ ስምምነቶች ማዕቀፍ ስፔን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የልማት ትብብር ለማጠናክር እንደምትሰራ አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በትብብር ሊሰሩባቸው የሚችሉ ሌሎች መስኮችን በማፈላለግ የሁለቱን ሀገራት ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ማጠናከር ይገባል ማለታቸው ከሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.