Fana: At a Speed of Life!

የብራዚል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እንደሚፈልጉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ እድሎችን የሚያስተዋውቅ መድረክ በብራዚል ብራዚሊያ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ÷ኢትዮጵያ ባላት ጂኦግራፊያዊ አቀማጥ  ለንግድ ትስስር ምቹ ሀገር መሆኗን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ምቹ ፖሊሲዎች መኖራቸውን ጠቁመው÷የብራዚል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የብራዚል ባለሃብቶች በበኩላቸው ÷በኢትጵያ በኢንቨስትመንት፣ በንግድና ቱሪዝም ዘርፍ በትብብር ለመስራት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.