Fana: At a Speed of Life!

ሦስት ብሔራዊ የቢዝነስ ፖርታሎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘርፈ-ብዙ የመንግሥት አገልግሎትን በኦንላይን ለማግኘትና ግልፅነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ሦስት የቢዝነስ ፖርታሎች ይፋ ተደረጉ፡፡

በባሕር ዳር፣ አዳማ እና ድሬዳዋ ከተሞች የሚተገበሩት እነዚህ ፖርታሎች፤ ለከተሞቹ የስማርት ሲቲ ዕቅድ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

ለሕብረተሰቡ ዘመናዊ አገልግሎትን በመስጠት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማጎልበት ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ፤ ካለፉት ዓመታት ልምድ በመውሰድና የቴክኖሎጂ እድገትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዘርፉ የበላይነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

የቢዝነስ ፖርታሉ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በአውሮፓ ሕብረት ትብብር በአዲስ አበባ ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን የሚኒስቴሩ መረጃ አስታውሷል፡፡

ፖርታሉ አዳዲስ ቢዝነስ ለሚጀምሩ አካላት የተቀናጀ አገልግሎት በመስጠት የንግድ ሥራ ቅልጥፍናን ይጨምራል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.