Fana: At a Speed of Life!

የአሁኑ ትውልድ በክሕሎታችን ብቻ ኢትዮጵያን ማነጽ እንችላለን – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሁኑ ትውልድ የሕይወት መስዋዕትነት መክፈል ሳይጠበቅብን በክሕሎታችን ብቻ ኢትዮጵያን ማነጽ እንችላለን ሲሉ የሥራና ክሕሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀውን “ክህሎት ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት መድረክ ከፍተዋል።

በዚህ ወቅትም ስለክሕሎትና ስለኢትዮጵያ ለብቻ የሚወጧቸው ጉዳዮች ሳይሆኑ አብሮነትን የሚጠይቁ ተግባራት መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአሁኑ ትውልድ የሕይወት መስዋዕትነት መክፈል ሳይጠበቅብን በክህሎታችን ብቻ ኢትዮጵያን ማነጽ እንችላለን ሲሉም ገልጸዋል።

ስለኢትዮጵያ መነጋገር የተለያ ስሜት እንደሚሰጥ አውስተው÷ሀገር ለመስራትና የራሳችንን ዓድዋ ለመፍጠር ምን ማድረግ እንዳለብን ተጨባጭ እውቀት የምናገኝበት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች እየሰለጠኑ እንደሚገኙም ነው የጠቆሙት።

የሥራና ክሕሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተሻላ በሬቻ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ጥራት ያለው ክሕሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እና ወደ ገበያ መር ለመቀየር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከኢንዱስትሪው እና ከግል ሴክተሩ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ ተግብር ተኮር ስልጠናን እውን ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በአጫጭር ስልጠና ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎች በመደበኛው ደግሞ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች የሚያልፉ ቢሆንም፤ የክሕሎት ልማቱን ከዚህ በላይ ለማሳደግ በትብብር መስራትን ይጠይቃል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.