Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ከስግደት ለሚመለሱ ክርስቲያን ምዕመናን ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ከስግደት ለሚመለሱ የክርስትና እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ አጋርተዋል።

የስቅለት በዓል ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በድሬዳዋ በሚገኙ የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በስግደት፣ በዝማሬ፣ በፀሎት እና በንስሃ ታስቦ ውሏል።

የእስልምና ኃይማኖት አባቶችና ተከታዮች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ደጃፎች ከስግደት ለሚመለሱ የክርስትና እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ በማጋራት አብሮነታቸውን አሳይተዋል።

በማዕድ ማቋደሱ ሥነ-ሥርዓት ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የተመራና የአስተዳደሩን ካቢኔ አባላት ያካተተው ቡድን መሳተፉ ተመላክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.